እ ………………..
ክበር ተመስገን ተመስገን
ኦሪት ላይሻር ሊታደስ
ዳግም ለፈካ ዘርቶ ነብስ
ሆኖ የማያውቅ ታየ ገድል
ጌታ ተገኘ ከድንግል
ወዳጄ ………
በምድር ቢበዛም የሰው ጣጣ
ዳግም እንዳይኖር የአምላክ ቁጣ
ሃጥያት እንዲሻር በእምነት
ሊሞት ተላከ ልጅ አባት
እ …………………..
እኔን ወዳጄ ምነው …ወዳጄ
ሰው ተበላሽቶ በምግባር
ሲኖር በዝሙት በስካር
እግዚአብሔር ልጁን ላከለት
አጥያቱ እንዲሻር በስቅለት
በቤተመቅደስ ከታየው
ከተለኮሰው
ጧፍ ሻማው
ከከርቤም ሆነ ከሽቶው
እጣኑን ጌታን ወደደው
ና ምነው …..
እ …………………..
ክበር ተመስገን ጌታችን
ነብሱን ከስጋው ያስበለጠ
ለጌታ ሊያድር የቆረጠ
አለምን ንቋት እንደዋዛ
አዩት በጉልበት ላብ ተገዛ
ከሰው ቤት ስራን ተቀጥረን
ሳናስብ ጥፋት አጠፍን
እንለምን እንዲ ተደፍተን
ጌታችን ደጉ ቢምረን
ወዳጄ ………
ብጎሳቆልም ጠንቶ ህመሜ
ባጉል ቢነሳም መልካም ስሜ
ገና እኖራለው አልሞት
አለልኝ አለም መድሃኒት
ወዳጄ ..
misganlove
ReplyDeleteyamral
ReplyDelete