መሪጌታ ፍቅሩ ዘለሰኛ መዝሙር 1
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድሃኒት
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
በቅሎና ግመል አዘጋጅቶ
ማልዶ እንደመሄድ አንግቶ
ምነው ወጣቶች በረሩ
ፈረስ ፈረስ እያሉ
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
ተጣልቻለው ከአምላክ ጋራ
በብዙም በደል በአንድ እንጀራ
እሱ እንኳን አይበላ ሆድ የለው
ከለከለኝ ምነው
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
ወልደ አምላክ እንኩዋን መሞቱ
ለኛ ብሎ ነው ለፍጥረቱ
በመለኮቱ ይነሳል
አብነቱን ያውቃል
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
ሰው ሲጠራ ለግብር
አንቀላፍቼ ነበር
ከንቱ ጌታዬን አማሁኝ
በትንሳኤው ላይረሳኝ
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
ውሃና ዘሩን ተሸክሜ
ምነው እያየ ደክሜ
ብትጠቁመኝ መንገዱን
አልፎ መሄጃውን
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
መንገድ ጠቋሚ ሳይኖር
መንታ መንገድ ላይ ስችገር
የግራው መንገድ ይቅርብኝ
እባክህ ምራኝ በቀኝ
እ …………………..
ስማኝ አምላኬ ምነው
የቀድሞ ሰዎች ሲበድሉ
በጥፋት ውሃ ተበሉ
እኛ ግን ቃልህ ስላለን
ከጥፋት እንድናለን
kalehiwot yasemalen!!!
ReplyDeletesteve gr 5 gold - Titanium Art
ReplyDeleteThis is the new 4x8 sheet metal prices near me gold model of the steve gr and it's a classic titanium comb gold look titanium damascus knives to you with the high quality of 1xbet 먹튀 an alloy in the center. The platinum titanium screws